1 ነገሥት 3:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጇ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርሷ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርሷም አይሁን! ለሁለት ይቆረጥ!” አለች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች። ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ደኅነኛውም ሕፃን የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ታውኳልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይደለም፤ ደኅነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ መግደልስ አትግደሉት” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛዪቱ ግን፥ “አካፍሉን እንጂ ለእኔም ለእርስዋም አይሁን” አለች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ደኅነኛውም የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ናፍቆአልና “ጌታዬ ሆይ! ደኀነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ አትግደል፤” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛይቱ ግን “ይከፈል እንጂ ለእኔም ለአንቺም አይሁን፤” አለች። See the chapter |