1 ነገሥት 22:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ኢዮሣፍጥንም “በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ለመዝመት ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢዮሣፍጥም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ስለዚህ ኢዮሣፍጥን፣ “በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ላይ ለመዝመት ዐብረኸኝ ለመሄድ ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ፣ “እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፣ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ኢዮሣፍጥንም “በራሞት ላይ አደጋ ለመጣል ከእኔ ጋር ለመዝመት ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮሣፍጥም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 የእስራኤል ንጉሥም ኢዮሣፍጥን፥ “በሬማት ዘገለዓድ እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” አለው። ኢዮሣፍጥም ለእስራእል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ኢዮሣፍጥንም “በሬማት ዘገለዓድ እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትመጣለህን?” አለው። ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው አለው። See the chapter |