1 ነገሥት 22:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ ከቁስሉም የሚፈሰው ደም ብዛት ከስር በኩል ሠረገላውን በክሎት ነበር፤ በዚያውም ቀን ምሽት ሞተ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም35 ጦርነቱም ቀኑን ሙሉ ተፋፍሞ ዋለ፤ በዚህ ጊዜ ንጉሡ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ቀና ብሎ እንደ ተደገፈ ነበር፤ የቍስሉ ደም በሠረገላው ወለል ላይ ይወርድ ነበር፤ በዚያ ዕለት ማታም ንጉሡ ሞተ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ ከቊስሉም የሚፈሰው ደም ብዛት ከስር በኩል ሠረገላውን በክሎት ነበር፤ በዚያውም ቀን ምሽት ሞተ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 በዚያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ ንጉሡም ከጥዋት እስከ ማታ በሶርያውያን ፊት በሰረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ የቍስሉም ደም በሰረገላው ውስጥ ፈሰሰ፤ ማታም ሞተ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 በዚያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ ንጉሡም በሶርያውያን ፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ ማታም ሞተ፤ የቍስሉም ደም በሠረገላው ውስጥ ፈሰሰ። See the chapter |