Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 2:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሽምዒን አስጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በዚህ በኢየሩሳሌም የራስህን መኖሪያ ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ከዚያ ወደየትም አትሂድ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዚያም ንጉሡ ሳሚን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በኢየሩሳሌም ቤት ሠርተህ እዚያው ተቀመጥ፤ ከዚያ ግን የትም እንዳትሄድ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሽምዒን አስጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “በዚህ በኢየሩሳሌም የራስህን መኖሪያ ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ከዚያ ወደየትም አትሂድ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ንጉ​ሡም ልኮ ሳሚን አስ​ጠ​ራ​ውና እን​ዲህ አለው፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤት ሠር​ተህ ተቀ​መጥ፤ ወዲ​ህና ወዲ​ያም አት​ውጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ንጉሡም ልኮ ሳሚን አስጠራውና “በኢየሩሳሌም ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ወዲህና ወዲያም አትውጣ።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 2:36
7 Cross References  

ጠቢብ ንጉሥ ኀጥኣንን በመንሽ ይበትናቸዋል፥ መንኰራኵሩንም በእነርሱ ላይ ያንኰራኩርባቸዋል።


በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ ይበትናል።


ንጉሡ ሰሎሞንም ላከ፥ ከመሠዊያውም አወረዱት፥ መጥቶም ለንጉሡ ለሰሎሞን እጅ ነሣ፥ ሰሎሞንም፦ “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።


አቤሴሎምም በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ሙሉ የንጉሡን ፊት ሳያይ ተቀመጠ።


ንጉሡ ግን፥ “እዚያው ቤቱ ይሂድ፤ ፊቴን ማየት የለበትም” አለ። ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ፊት ቀርቦ አልታየም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements