1 ነገሥት 18:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም44 በሰባተኛው ጊዜ አገልጋዩ፣ “እነሆ፤ የሰው እጅ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው” አለው። ኤልያስም፣ “ሂድና አክዓብን፣ ‘ዝናቡ ሳያግድህ፣ ሠረገላህን ጭነህ ውረድ’ ብለህ ንገረው” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)44 በሰባተኛውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕር ውኃ ቋጥራ ስትወጣ አየሁ” አለ። እርሱም፥ “ወጥተህ አክዓብን፦ ዝናብ እንዳይዝህ ሰረገላህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)44 በሰባተኛውም ጊዜ “እነሆ፥ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጣች፤” አለ። እርሱም “ወጥተህ አክዓብን ‘ዝናብ እንዳይከለክልህ ሠረገላን ጭነህ ውረድ፤’ በለው፤” አለ። See the chapter |