1 ነገሥት 14:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ንብረትና የቤተ መንግሥቱን ንብረት ዘርፎ ወሰደ፤ ሰሎሞን ያሠራው የወርቅ ጋሻ፤ ሰሎሞን ያሠራቸው የወርቅ ጋሻዎች ሁሉ እንኳ ሳይቀሩ ሁሉንም ነገር አጋዘ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊትም ከሱባ ንጉሥ ከአድርዓዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸውን የወርቅ ጦሮችና ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የእግዚአብሔርም ቤተ መዛግብትንና የንጉሥ ቤተ መዛግብትን ወሰደ፤ ሁሉንም ወሰደ፤ ሰሎሞንም የሠራውን የወርቁን ጋሻ ሁሉ ወሰደ። See the chapter |