1 ነገሥት 13:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ሽማግሌው ነቢይ ግን፣ “እኔም እኮ እንደ አንተው ነቢይ ነኝ፤ መልአክ በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘እንጀራ እንዲበላና ውሃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው’ ብሎኝ ነው” አለው፤ ነገር ግን ውሸቱን ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው ግን በመዋሸት ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እርሱም “እኔ ደግሞ እንደ አንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም ‘እንጀራ ይበላ ዘንድ ውሃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው፤’ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ፤” አለው። ዋሽቶም ተናገረው። See the chapter |