1 ነገሥት 12:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃው ምስል መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 በይሁዳ እንደሚደረገው ሁሉ ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በዓል እንዲሆን ወሰነ፤ በመሠዊያውም ላይ መሥዋዕት አቀረበ። ለሠራቸው ጥጆች መሥዋዕት በማቅረብም እንዲህ ያለውን ድርጊት በቤቴል ፈጸመ። በማምለኪያ ኰረብቶች ላይ ላሠራቸው አብያተ ጣዖታት በቤቴል ካህናቱን መደበ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዐይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምስሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤቴል ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን እነዚያን ካህናት በቤቴል አኖራቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 በስምንተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛውም ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ በመሠዊያውም ላይ ሠዋ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ እንዲሁ በቤቴል አደረገ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን ካህናት በቤቴል አኖራቸው። See the chapter |