Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ የጦር አዛዡ ኢዮአብ የሞቱትን ለመቅበር ወጥቶ የኤዶማውያንን ወንዶች ልጆች ሁሉ ፈጅቶ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያ በፊት ዳዊት ከኤዶም ጋራ በተዋጋ ጊዜ፣ የሞቱትን ለመቅበር መጥቶ የነበረው የሰራዊቱ አዛዥ ኢዮአብ የኤዶምን ሰዎች ሁሉ ፈጅቶ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ የጦር አዛዡ ኢዮአብ የሞቱትን ለመቅበር ወጥቶ የኤዶማውያንን ወንዶች ልጆች ሁሉ ፈጅቶ ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15-16 ኢዮአብና እስራኤልም ሁሉ የኤዶምያስን ወንድ ሁሉ እስኪገድሉ ድረስ ስድስት ወር በዚያ ተቀምጠው ነበርና ዳዊት በኤዶምያስ በነበረ ጊዜ፥ የሠራዊቱም አለቃ ኢዮአብ ተወግተው የሞቱትን ሊቀብር በወጣ ጊዜ፥ የኤዶምያስንም ወንድ ሁሉ በገደለ ጊዜ፥

See the chapter Copy




1 ነገሥት 11:15
14 Cross References  

በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ ጌታም ዳዊት በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።


አምላክህ ጌታ አሳልፎ በእጅህ በሰጠህ ጊዜ፥ በውስጧ ያሉትን ወንዶች በሙሉ በሰይፍ ግደላቸው።


ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፥ በፍልስጥኤም ላይ ድሌን ዐውጃለሁ።


ለመዘምራን አለቃ፥ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ።


አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ።


በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ፥ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለህ።”


ጌታም እንዲህ አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱም ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል።”


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ።


ስለዚህም ጌታ የኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ ወገን የሆነውን ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት።


ኢዮአብና የእስራኤል ሠራዊት የኤዶምን ወንዶች ልጆች ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ ስድስት ወራት በዚያ ቆይተዋል።


ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements