1 ነገሥት 10:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ሰሎሞንም ለሰረገሎቹ ዐራት ሺህ እንስት ፈረሶች ነበሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞችም ነበሩት፤ በሰረገሎችም ከተሞች ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው። ሰሎሞንም ከወንዙ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብፅ ድንበር ድረስ በነገሥታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሠረገሎችም ከተሞች ከንጉሡም ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው። See the chapter |