Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ብትለይም ሳታገባ ለብቻዋ ትኑር፤ ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ፤ እንዲሁም ባል ሚስቱን አይፍታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር፤ አለዚያ ከባሏ ጋራ ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን አይፍታት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ብትለይም ሳታገባ ለብቻዋ ትኑር፤ ወይም ከባልዋ ጋር ትታረቅ፤ እንዲሁም ባል ሚስቱን አይፍታ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከተ​ፋ​ታ​ችም ብቻ​ዋን ትኑር፤ ያለ​ዚያ ከባ​ልዋ ጋር ትታ​ረቅ፤ ባልም ሚስ​ቱን አይ​ፍታ።

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 7:11
10 Cross References  

እነሆ፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ብትሄድ ሌላም ወንድ ብታገባ፥ በውኑ በድጋሚ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ያች ምድር እጅግ የረከሰች አትሆንምን? አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል ጌታ።


ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባሏ አትለይ፤


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።


በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል በማስከፈል ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፥ እርሷም ሚስቱ ሆና ትኑር፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።”


አንዳንድ ፈሪሳውያንም መጥተው፥ “ሰው ሚስቱን መፍታት ይገባዋልን?” ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።


እርሷም ባሏን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች” አላቸው።


“ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባልዋም የፈታትን የሚያገባ ያመነዝራል።


ሌሎችንም፥ ጌታም አይደለም፥ እኔ እላለሁ፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር፥ እርሷም ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ፥ አይፍታት፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements