Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንግዲህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ሆነ ወይም የሚያጠጣ ቢሆን ምንም አይደለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ ለሥራው ዋና የሆነው ተክሉን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው እንጂ የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ ምንም አይደለም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም የሚ​ተ​ክ​ልም ቢሆን፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም ቢሆን የሚ​ጠ​ቅ​መው ነገር የለም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 3:7
12 Cross References  

እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።


አንድ ሰው ምንም ሳይሆን አንድ ነገር የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።


እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ።


ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ።


ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።


እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ ሥራቸውም ምንም ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።


አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምንም እንደሚያንሱ፥ እንደ ባዶ ነገር ይቈጠራሉ።


የጌታ አምላካችን ቸርነት በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።


እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤


የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል።


በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements