1 ቆሮንቶስ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ወንድሞች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ የእግዚአብሔርን ምስጢር በቃላት መራቀቅ ወይም ጥበብ ለእናንተ ለማወጅ አልመጣሁም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር የመሰከርኩት የንግግርን ችሎታና የፍልስፍናን ጥበብ በማሳየት አይደለም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። See the chapter |