1 ቆሮንቶስ 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እንደዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ፣ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው የዋሽንት ወይም የበገና ድምፅ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እንደ ዋሽንትና እንደ ክራር ያሉት ነፍስ የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የተለየ የድምፅ ቅኝት ከሌላቸው የሚሰጡት የሙዚቃ ድምፅ ምን መሆኑ እንዴት ይታወቃል? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ነፍስ የሌለው ድምፅ የሚሰጥ እንደ መሰንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣሪያ በስልት ካልተመታ መሰንቆው ወይም ክራሩ የሚለውን ማን ያውቃል? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል? See the chapter |