Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 14:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፥ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በቤተ ክርስቲያን መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 አንዳንድ ነገርን ማወቅ ቢፈልጉ ባሎቻቸውን በቤታቸው ይጠይቁ፤ በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ሴት እንድትናገር ተገቢ አይደለም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ለሴት በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን መና​ገር ክል​ክል ነው፤ ሊማሩ ከወ​ደዱ ደግሞ በቤ​ታ​ቸው ባሎ​ቻ​ቸ​ውን ይጠ​ይቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 14:35
7 Cross References  

እናንተም ባሎች ሆይ! ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ ከሚስቶቻችሁ ጋር በመተሳሰብ ኑሩ፤ የሕይወትንም ጸጋ አብረዋችሁ ስለሚወርሱ እንደ ደካማነታቸው ሴቶችን አክብሯቸው።


እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል።


ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?


ሴትም ራስዋን የማትከናነብ ከሆነ ደግሞ ጠጉርዋን ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።


ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤


የእግዚአብሔር ቃል የወጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነውን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements