Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 14:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፥ በባዕዳንም አንደበት ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፥ ይላል ጌታ” ተብሎ በኦሪትም ተጽፎአል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በሕግም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፣ በባዕዳንም አንደበት፣ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፤” ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህም፦ “ ‘በተለያዩ ቋንቋዎች በሚናገሩ ሰዎችና በባዕድ ሰዎች አፍ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በኦ​ሪ​ትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌ​ሎች ቋን​ቋ​ዎ​ችና በሌላ አን​ደ​በት እና​ገ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዲ​ሁም ሆኖ አይ​ሰ​ሙ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ​አል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሌሎችን ልሳኖች በሚናገሩ ሰዎችና በሌላ አንደበት ለዚህ ሕዝብ እነግራቸዋለሁ፥ እንዲህም ቢሆን አይሰሙኝም ይላል ጌታ ተብሎ በሕግ ተጽፎአል።

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 14:21
7 Cross References  

ጌታ እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋው የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤


የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ጽኑ ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።


ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤


ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ፤’ ተብሎ በሕጋችሁ ተጽፎ የለምን?


በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።


ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements