1 ቆሮንቶስ 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ፥ የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለምን? የምንቆርሰውስ ኀብስት፥ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለምን? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋራ ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋራ ኅብረት ያለው አይደለምን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን የምንካፈለው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰው ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ይህ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር አንድ አይደለምን? የምንፈትተው ይህስ ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይደለምን? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? See the chapter |