1 ቆሮንቶስ 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው መመዘኛ ብዙዎች ጥበበኞች አልነበሩም፥ ብዙዎች ኀያላን አልነበሩም፥ ብዙዎች ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ወንድሞች ሆይ፤ በተጠራችሁ ጊዜ ምን እንደ ነበራችሁ እስኪ አስቡ። በሰው መስፈርት ከእናንተ ብዙዎቻችሁ ዐዋቂዎች አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ኀያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከትልቅ ቤተ ሰብ አልተወለዳችሁም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በጠራችሁ ጊዜ ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እንደ ሰው አስተሳሰብ ከእናንተ መካከል ብዙዎች ጥበበኞች ወይም ብርቱዎች ወይም ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ወንድሞቻችን! እንግዲህ እንዴት እንደ ተጠራችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙዎች ዐዋቂዎች አይደላችሁምና፥ ብዙዎች ኀያላንም አይደላችሁምና፥ በዘመድም ብዙዎች ደጋጎች አይደላችሁምና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። See the chapter |