1 ዜና መዋዕል 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ አባቶቻቸውም የጌታን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ እንደ ነበር እንዲሁ የድንኳኑን የመግቢያ ደጅ ይጠብቁ ነበር።። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የኤቢያሳፍ የልጅ ልጅ የቆሬ ልጅ ሻሉም የቆሬ ጐሣ አባሎች ከሆኑት ከሌሎች ዘመዶቹ ጋር በመሆን የቀድሞ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሰፈር ይጠብቁ በነበረው ዐይነት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳንኑም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር። See the chapter |