1 ዜና መዋዕል 7:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በጦርነት ላይ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሀያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተሰብ አለቆች፥ ዝነኛ ጦረኞችና ምርጥ የሆኑ መሪዎች ነበሩ፤ የአሴር ዘሮች ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑ ኻያ ስድስት ሺህ ወንዶች ነበሩአቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በሰልፍ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን፥ ኀያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በሰልፍ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ። See the chapter |