1 ዜና መዋዕል 7:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለውግያ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እነርሱ ብዙ ሚስቶችና ብዙ ልጆች ስለ ነበሩአቸው ዘሮቻቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱ ሠላሳ ስድስት ሺህ ወንዶች ማቅረብ ይችሉ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤት ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ። See the chapter |