Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ዜና መዋዕል 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሽሙኤል፥ የአባታቸውም የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቁጥራቸው ሀያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የቶላ ወንዶች ልጆች፤ ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ቶላዕ ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዑዚ፥ ረፋያ፥ ይሪኤል፥ ያሕማይ፥ ዩብሳምና ሸሙኤል ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም የቶላዕ ጐሣ ቤተሰቦች አለቆችና ዝነኛ ወታደሮች ነበሩ፤ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የእነርሱ ዘሮች ብዛት ኻያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የቶ​ላም ልጆች፤ ኦዚ፥ ረፋያ፥ ይሪ​ኤል፥ የሕ​ማይ፥ ይብ​ሣም፥ ሰሙ​ኤል፥ የአ​ባ​ታ​ቸው የቶላ ቤት አለ​ቆች፥ በት​ው​ል​ዳ​ቸው ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳ​ዊት ዘመን ቍጥ​ራ​ቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የቶላም ልጆች ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሽሙኤል፤ የአባታቸውም የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።

See the chapter Copy




1 ዜና መዋዕል 7:2
5 Cross References  

የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ምደባ ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉት ሹማምንት እንደ ቁጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ውስጥ ባሉት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።


የይሳኮርም ልጆች፥ ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ ሺምሮን፥ አራት ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements