1 ዜና መዋዕል 4:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 በስማቸው የተጻፉ እነዚህም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበርና በስፍራቸው ተቀመጡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ። See the chapter |