1 ዜና መዋዕል 27:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዛሞት ሹም ነበረ፤ በአገሩም በከተሞቹም በመንደሮቹም በግንቦቹም ባሉ ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤ የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25-31 የቤተ መንግሥት ንብረት ኀላፊዎች የሆኑት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ የዐዲኤል ልጅ ዓዝማዌት በየገጠሩ፥ በየከተማው፥ በየመንደሩ በየምሽጉ የሚገኙ የመንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የዑዚያ ልጅ ዮናታን የግብርና ሥራ ኀላፊ፦ የከሉብ ልጅ ዔዝሪ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ የራማ ተወላጅ የሆነው ሺምዒ የወይን ጠጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የሸፋም ተወላጅ የሆነው ዛብዲ በደቡባዊ ኰረብቶች የሚገኙት የወይራና የወርካ ዛፎች ኀላፊ፦ የጌዴር ተወላጅ የሆነው ባዓልሐናን የወይራ ዘይት ግምጃ ቤት ኀላፊ ኢዮአስ በሳሮን ሜዳ የሚገኙት የቀንድ ከብቶች ኀላፊ የሳሮን ተወላጅ የሆነው ሺጥራይ በሸለቆዎች የሚገኙ የቀንድ ከብቶች አስተዳዳሪ፦ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ የግመሎች ኀላፊ፦ እስማኤላዊው ኦቢል የአህዮች ኀላፊ፦ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ዬሕድያ የበጎችና የፍየሎች ኀላፊ፦ ሀግራዊው ያዚዝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዳኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ፤ በሜዳውም፥ በከተሞቹም፥ በመንደሮቹም፥ በግንቦቹም ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዛሞት ሹም ነበረ፤ በሜዳውም በከተሞችም በመንደሮችም በግንቦችም ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤ See the chapter |