1 ዜና መዋዕል 27:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቁጣ ወረደ፥ ቁጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሕዝብ ቈጠራ ማድረግ ጀምሮ ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፤ በዚህ በሕዝብ ቈጠራ ምክንያት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ቀጥቶ ስለ ነበር የመጨረሻው ቊጥር በንጉሥ ዳዊት መንግሥት የታሪክ መዝገብ ውስጥ አልተመዘገበም ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም መቍጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህ ነገር በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት የታሪክ መጽሐፍ አልተጻፈም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፥ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም። See the chapter |