1 ዜና መዋዕል 26:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ንጉሥ ዳዊት ከእነዚያ ዘመዶች መካከል ምርጥ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ የቤተሰብ አለቆችን መረጠ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ማለትም በሮቤል፥ በጋድና በምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛቶች መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ጉዳይ ሁሉ የማስተዳደር ኀላፊነት ሰጣቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ቃል ሁሉና በንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ በሮቤላውያንና በጋዳውያን፥ በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኵሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው። See the chapter |