Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ዜና መዋዕል 26:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ ሥልጣን በታች ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ባለራእዩ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አበኔር፣ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የቀደሱትን ሁሉና እንዲሁም ሌሎቹን ንዋያተ ቅድሳት ሰሎሚትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሸሎሚትና ዘመዶቹ ለቤተ መቅደስ ሥራ ለተለዩ ነገሮች ሁሉ፥ በነቢዩ ሳሙኤል፥ በንጉሥ ሳኦል፥ በኔር ልጅ አበኔርና በጸሩያ ልጅ ኢዮአብ ላቀረቡአቸው ስጦታዎች ጭምር ኀላፊዎች ነበሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ነቢዩ ሳሙ​ኤል፥ የቂ​ስም ልጅ ሳኦል፥ የኔ​ርም ልጅ አበ​ኔር፥ የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ የቀ​ደ​ሱት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንዋየ ቅድ​ሳት ሁሉ ከሰ​ሎ​ሚ​ትና ከወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ በታች ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ እጅ በታች ነበረ።

See the chapter Copy




1 ዜና መዋዕል 26:28
7 Cross References  

ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።


ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።


በጦርነትም ከተገኘው ምርኮ የጌታን ቤት ለመሥራት ስጦታ ቀድሰው ሰጡ።


ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች እንዲሆኑ በውጭው በሚከናወነው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።


ደግሞም ለጌታ ቤት አደባባዮችና በዙሪያው ለሚሆኑ ጓዳዎች፥ ለእግዚአብሔርም ቤት ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት፥ ለንዋየ ቅድሳቱም ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ያሰበውን ንድፈ ሐሳብ ሁሉ ሰጠው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements