1 ዜና መዋዕል 26:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በጌታ ቤት እንዲያገለግሉ በየአለቆቻቸው የደጁ ጠባቂዎች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ ቤተ ዘመዶቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናወን ምድብ ተራ ነበራቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች በየቤተሰቡ በቡድን ተከፍለው ነበር፤ እነርሱም ልክ እንደ ሌሎቹ ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገልግሎት ነበራቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች በየሰሞናቸው የሚጠብቁ እነዚህ ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገልግሉ ዘንድ የበረኞች የአለቆች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ። See the chapter |