Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ዜና መዋዕል 26:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የደጁም ጠባቂዎች ምድባቸው እንደዚህ ነበር፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ ሌዋውያን የሥራ ምድብ እንደሚከተለው ነው፦ ከቆሬ ጐሣ ከአሳፍ ቤተሰብ የቆሬ ልጅ መሼሌምያ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በረ​ኞ​ችም እን​ደ​ዚህ ተመ​ደቡ፤ ከቆ​ሬ​ያ​ው​ያን ከአ​ሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱ​ላም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም።

See the chapter Copy




1 ዜና መዋዕል 26:1
15 Cross References  

ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።


በማናቸውም ነገር ሁሉ ርኩስ የሆነ ሰው እንዳይገባ በጌታ ቤት በር በጠባቂዎችን አኖረ።


ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።


የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥


ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ወጣ፤ ልጆቹም ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።


ሜሱላም ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በኩሩ ዘካርያስ፥ ሁለተኛው ይዲኤል፥ ሦስተኛው ዮዛባት፥ አራተኛው የትኒኤል፥


የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።


ከሌዋውያንም የሜራሪ ልጆች የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሸማያ ነበር፤


አራቱ ሺህም የደጁ ጠባቂዎች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለምስጋና በተሰሩት በዜማ ዕቃዎች ጌታን ያመሰግኑ ነበር።


ለሜሱላም ኃያላን የነበሩ ዐሥራ ስምንት ልጆችና ወንድሞች ነበሩት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements