1 ዜና መዋዕል 17:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት የሆነ ነገር ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባርያህ ቤት ደግሞ ስለ ወደ ፊቱ ሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 አምላክ ሆይ፤ ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቈጥረህ ስለ ወደ ፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገርህ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ያለፈው ሁሉ በፊትህ የማይበቃ ሆኖ ስለ አገልጋይህ ቤት ለሚመጣው ሩቅ ዘመን አሁንም እንደገና እኔን እንደ ትልቅ ባለማዕርግ አድርገህ ተመለከትከኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። See the chapter |