1 ዜና መዋዕል 17:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ንጉሡም ዳዊት ገባ፥ በጌታም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፦ “አቤቱ አምላክ ሆይ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድነው? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለመሆኑ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን ሄደ፤ ተቀምጦም እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔ ይህን ሁሉ ነገር ታደርግልኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ለዘለዓም የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ “አቤቱ አምላክ ሆይ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው? See the chapter |