Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ዜና መዋዕል 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ ከእርሱ ላይ ከቶውንም አልወስድም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንዳራቅሁ ሁሉ፣ ከርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ አንተ በሳኦል እግር ተተክተህ ትነግሥ ዘንድ ከዙፋኑ ባወረድኩት በሳኦል ላይ ባደረግሁት ዐይነት ምሕረቴን ከልጅህ በማራቅ አልተወውም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጄ ይሆ​ነ​ኛል፤ ከአ​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት እን​ዳ​ራ​ቅሁ፥ ምሕ​ረ​ቴን ከእ​ርሱ አላ​ር​ቅም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበረው እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።

See the chapter Copy




1 ዜና መዋዕል 17:13
16 Cross References  

ከመላእክትስ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ደግሞም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤”


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ትእዛዙን እናገራለሁ፥ ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”


እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘለዓለም አጸናለሁ።


ጌታንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


“ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤” ይላል ሁሉንም የሚገዛ ጌታ።


አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።


ከደመናውም፦ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


እርሱ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤


ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።


በቤቴና በመንግሥቴም ለዘለዓለም አቆመዋለሁ፥ ዙፋኑም ለዘለዓለም ይጸናል።’ ”


Follow us:

Advertisements


Advertisements