1 ዜና መዋዕል 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ቀድሞም አልተሸከማችሁትምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና ጌታ አምላካችን በመካከላችን ቊጣውን አወረደ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የአምላካችን የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤ እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከዚህ በፊት እናንተ ተገኝታችሁ ታቦቱን ባለመሸከማችሁ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት ስላላገለገልነው አምላካችን እግዚአብሔር ቀጥቶናል።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በቀድሞ ሥራችን አምላካችን እግዚአብሔር እርስ በርሳችን አላጠፋንም፤ በጦር አልፈለገንምና” አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ቀድሞም አልተሸከማችሁምና፥ እንደ ሥርዐቱም አልፈለግነውምና አምላካችን እግዚአብሔር በመካከላችን ስብራት አደረገ፤” አላቸው። See the chapter |