1 ዜና መዋዕል 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት “ዙሪያውን ከብበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ ከኋላቸው በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ዳዊትም እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከኋላ በኩል ዞረህ በሾላ ዛፎች አጠገብ በመሆን አደጋ ጣልባቸው እንጂ በዚህ በኩል ሽቅብ ወጥተህ በመሰለፍ አደጋ አትጣልባቸው፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “አትውጣ፥ በኋላቸውም አትከተላቸው፤ ነገር ግን ከኋላቸው ዙረህ ቅረባቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ። See the chapter |