1 ዜና መዋዕል 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣ “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈራረሳቸው” አለ፤ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ስለዚህ ዳዊት ባዓልፈራጺም ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ ድል ካደረጋቸው በኋላ “የጠላትን ሠራዊት እንደ ጐርፍ ጥሼ እንዳልፍ እግዚአብሔር ረዳኝ” አለ፤ ከዚያም በኋላ ያ ስፍራ “ባዓልፈራጺም” ተብሎ ተጠራ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ወደ በኣልፐራሲምም ወጡ፤ በዚያም ዳዊት መታቸው። ዳዊትም “ውሃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው፤” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም “በኣልፐራሲም” ብለው ጠሩት። See the chapter |