1 ዜና መዋዕል 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ዳዊትም፦ “ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኮንን ይሆናል” አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣ አለቃም ሆነ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ዳዊትም፣ “ኢያቡሳውያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል” አለ፤ ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤ እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ዳዊትም “በመጀመሪያ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ የሚጥል ሰው የሠራዊቱ አዛዥ ይሆናል!” አለ፤ የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ሄዶ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ በመጣሉ የሠራዊቱ አዛዥ ሆነ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ዳዊትም “ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኮንን ይሆናል፤” አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣ፤ አለቃም ሆነ። See the chapter |