ዘካርያስ 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እኔም፦ እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው? አልሁ። እርሱም፦ አንድ ሰው ራሱን እስከማያነሣ ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፣ እነዚህ ግን ሊያስፈራሩአቸው፥ የይሁዳንም አገር ይበትኑ ዘንድ ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊጥሉ መጥተዋል ብሎ ተናገረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እኔም፣ “እነዚህስ ምን ሊያደርጉ መጡ?” አልሁ። እርሱም፣ “እነዚህ ቀንዶች ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እንዳይችል ይሁዳን የበታተኑ ናቸው፤ እነዚህ የእጅ ሙያተኞች ግን የመጡት እነርሱን ሊያስደነግጧቸው፣ ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን የእነዚህን የአሕዛብ ቀንዶች ሰብሮ ለመጣል ነው” አለኝ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እኔም “እነዚህ ሰዎች የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “እነርሱ የመጡት የይሁዳን ምድር ፈጽሞ አጥፍተው፥ ሕዝብዋ ተበታትኖ እንዲቀር ያደረጉትን የአሕዛብ መንግሥታት ለማሸበርና ለመጣል ነው” አለኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እኔም፦ እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው? አልሁ። እርሱም፦ አንድ ሰው ራሱን እስከማያነሣ ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፥ እነዚህ ግን ሊያስፈራሩአቸው፥ የይሁዳንም አገር ይበትኑ ዘንድ ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊጥሉ መጥተዋል ብሎ ተናገረ። Ver Capítulo |