ሩት 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እርሱም፦ የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው አላት፣ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት አሸከማትም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እንዲሁም፣ “በላይሽ የደረብሽውን ልብስ አቅርቢልኝ፤ ዘርግተሽም ያዢው” አላት፤ ዘርግታ እንደ ያዘችም ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፍሮ አሸከማት፤ ከዚያም ወደ ከተማ ተመለሰች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እርሱም፦ “የለበስሽውን ልብስ አምጥተሽ ያዥው” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፍሮላት አሸከማት። እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ቦዔዝም “ሸማሽን ከላይሽ አንሺና ወደዚህ ዘርጊው” አላት። እርስዋም ሸማዋን ዘረጋች፤ ቦዔዝም ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፈረላትና አንሥቶ በትከሻዋ አሸከማት። ከዚያም እርሱ ወደ ከተማ ሄደ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እርሱም “የለበስሽውን ኩታ አምጥተሽ ያዢው፤” አላት፤ በያዘችም ጊዜ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላት፤ አሸከማትም። Ver Capítulo |