Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ባራ​ቅ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የም​ገ​ባው ኪዳን ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ኀጢአታቸውንም ሳስወግድ፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኃጢአታቸውንም በደመሰስኩላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 11:27
12 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚያ ወራት በዚ​ያም ዘመን፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ዚ​ህን በም​ድር የተ​ረ​ፉ​ትን ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእ​ስ​ራ​ኤል በደል ይፈ​ለ​ጋል፤ አይ​ኖ​ር​ምም፤ የይ​ሁ​ዳም ኀጢ​አት ይፈ​ለ​ጋል፥ ምንም አይ​ገ​ኝም።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! በኀ​ጢ​አ​ትህ ወድ​ቀ​ሃ​ልና ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለስ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


“ከእ​ነ​ዚያ ወራ​ቶች በኋላ የም​ገ​ባ​ላ​ቸው ኪዳን ይህቺ ናት ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ባ​ቸው አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ ካለ በኋላ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos