Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር በሚ​ሞት ሰውና በዎ​ፎች፥ አራት እግር ባላ​ቸ​ውም፥ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም መልክ መስ​ለው ለወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የዘላለም አምላክን ክብር ምዉት በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ በእንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ መስለው ለወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የማይጠፋውን የእግዚአብሔርን ክብር በሚጠፋው በሰው፥ በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው እንስሳትና በመሬት ላይ በሚሳቡ እንስሳት መልክ ምስል ለወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የማያልፈውን እግዚአብሔርን በማክበር ፈንታ ኀላፊ በሆነው በሰው ምስል፥ በወፍ፥ አራት እግሮች ባሉአቸው እንስሶች፥ በመሬት ላይ በሚሳቡ እንስሶች መልክ ለተሠራው ምስል ክብርን ሰጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 1:23
16 Referencias Cruzadas  

ቃሉን ልኮ ፈወ​ሳ​ቸው፥ ከጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።


አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያል​ሆኑ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይለ​ውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብ​ራ​ቸ​ውን ለማ​ይ​ረባ ነገር ለወጡ።


እን​ግ​ዲህ እኛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ዶች ከሆን በሰው ዕው​ቀ​ትና ብል​ሀት በተ​ቀ​ረጸ በድ​ን​ጋ​ይና በብር፥ በወ​ር​ቅም አም​ላ​ክ​ነ​ቱን ልን​መ​ስ​ለው አይ​ገ​ባም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እው​ነት ሐሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ታ​ልና፤ ተዋ​ር​ደ​ውም ፍጥ​ረ​ቱን አም​ል​ከ​ዋ​ልና፤ ሁሉን የፈ​ጠ​ረ​ውን ግን ተዉት፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


እኔም ገባ​ሁና፥ እነሆ በግ​ንቡ ዙሪያ ላይ የተ​ን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች አዕ​ዋ​ፍና እን​ስ​ሳ​ትን ምሳሌ ከን​ቱና ርኩስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ጣዖ​ታት ሁሉ ተሥ​ለው አየሁ።


“በላይ በሰ​ማይ ካለው፥ በታ​ችም በም​ድር ካለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ካለው ነገር ማን​ኛ​ው​ንም ምሳሌ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ፤


ጠራ​ቢ​ውም እን​ጨት ቈርጦ በልኩ ያቆ​መ​ዋል፤ በማ​ጣ​በ​ቂ​ያም ያያ​ይ​ዘ​ዋል፤ በሰው አም​ሳ​ልና በሰው ውበት ያስ​መ​ስ​ለ​ዋል፤ በቤ​ትም ውስጥ ያቆ​መ​ዋል።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማን ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስ​ተ​ያ​ዩ​ታ​ላ​ችሁ?


ቀድ​ሞም እና​ንተ አሕ​ዛብ በነ​በ​ራ​ችሁ ጊዜ ዲዳ​ዎች ጣዖ​ታ​ትን ታመ​ልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖ​ትም በማ​ም​ለክ ረክ​ሳ​ችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰ​ዱ​አ​ች​ሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ዐይ​ና​ች​ሁን ወደ ሰማይ አን​ሥ​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈ​ጠረ ማን ነው? ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሙሉ የሚ​ቈ​ጥ​ራ​ቸው እርሱ ነው፤ በየ​ጊ​ዜ​ያ​ቸው ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ሁሉ​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ በክ​ብሩ ብዛ​ትና በች​ሎቱ ብር​ታት አን​ድስ እንኳ አይ​ታ​ጣ​ውም።


በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤


በው​ስ​ጡም አራት እግር ያለው እን​ስሳ ሁሉ፥ አራ​ዊ​ትም፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም፥ የሰ​ማ​ይም ወፎች ነበ​ሩ​በት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios