Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አምስትም ወር ሊያሰቃዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚያሠቃዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚያሠቃይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እነርሱንም ዐምስት ወር ብቻ እንዲያሠቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሏቸው ሥልጣን አልተሰጣቸውም፤ የሚሠቃዩትም ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ሥቃይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለአምስትም ወር እንዲያሰቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሉአቸው አልተፈቀደላቸውም፤ እነርሱም የሚያደርሱት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚያደርሰው ስቃይ ዓይነት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነርሱንም ቢሆን አምስት ወር ለማሠቃየት እንጂ ለመግደል ፈቃድ አልተሰጣቸውም፤ አንበጣዎቹ የደረሰባቸው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ያለ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 9:5
12 Referencias Cruzadas  

እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “እነሆ፥ ሥጋ​ው​ንና አጥ​ን​ቱን በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ። ነገር ግን ሕይ​ወ​ቱን ተው።”


ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፤ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።


ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።


ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።


ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸውማል፤ ይገድላቸውማል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


አሁ​ንም አባቴ ከባድ ቀን​በር ጭኖ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” ብለው ነገ​ሩት።


“አባቴ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን እጨ​ም​ር​በ​ታ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ እንደ ብላ​ቴ​ኖቹ ምክር ተና​ገ​ራ​ቸው።


አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩር​ን​ች​ትና እሾህ ከአ​ንተ ጋር ቢኖ​ሩም፥ አን​ተም በጊ​ን​ጦች መካ​ከል ብት​ቀ​መጥ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ፍራ፤ አንተ ቃላ​ቸ​ውን አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios