Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሕያዋን ፍጡራኑ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ክብር፣ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ገናናነት ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እንስሶቹ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለሚኖረው ገናናነት፥ ክብርና ምስጋና በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 4:9
20 Referencias Cruzadas  

እን​ደ​ሰ​ማን እን​ዲሁ አየን፥ በሠ​ራ​ዊት ጌታ ከተማ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ታል።


እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም ይነ​ግ​ሣል።


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ዖዝ​ያን በሞ​ተ​በት ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ዥ​ምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ አየ​ሁት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ቤቱን ሞል​ቶት ነበር።


እጄን ወደ ሰማይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና፥ በቀኜ እም​ላ​ለሁ፦ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እኔ ሕያው ነኝ እላ​ለሁ።


ዘወ​ትር በእ​ርሱ በኩል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው ይቻ​ለ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ነውና ያስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ዋል።


በዚ​ህስ የሚ​ሞት ሰው ዐሥ​ራ​ትን ይቀ​በ​ላል፤ በወ​ዲ​ያው ግን ሕያው እንደ ሆነ መጽ​ሐፍ የሚ​መ​ሰ​ክ​ር​ለት እርሱ ይቀ​በ​ላል።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ


ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። ለእኔም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።


ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም ዙፋን በሰማይ ቆሞአል፤ በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤


አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።


በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።


ተራራዎችንና ዐለቶችንም “በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤


ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos