Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፤ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፤ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እነርሱም፣ ‘የተመኘሽው ፍሬ ከአንቺ ርቋል፤ ብልጽግናሽና ክብርሽ ሁሉ ጠፍቷል፤ ዳግመኛም ተመልሶ አይመጣም’ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ነፍስሽም የጎመጀችለት ፍሬ ከአንቺ ተለይቶ ሄዶአል፤ የድሎትና የጌጥ ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አይገኙም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነጋዴዎቹም “አንቺ የተመኘሻቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ከአንቺ ርቀው ሄደዋል፤ ሀብትሽም ጌጣ ጌጥሽም ሁሉ ጠፍቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነዚህን ሁሉ ከቶ አታገኚአቸውም!” ይሉአታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 18:14
12 Referencias Cruzadas  

እነ​ርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እን​ዳ​ን​መኝ እነ​ርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑ​ልን።


ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤


አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው።


ከጨ​ለ​ማና ከሞት ጥላ አወ​ጣ​ቸው፥ እግር ብረ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰበረ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል?


የጐ​መጁ ሕዝብ በዚያ ተቀ​ብ​ረ​ዋ​ልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃ​ብረ ፍት​ወት” ተብሎ ተጠራ።


ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።


ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።


እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios