Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንዲሁም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድኾች፣ ጌቶችና ባሮች ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲቀበሉ አስገደዳቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ታናናሾችና ታላላቆች፥ ሀብታሞችና ድሆች፥ ጌታዎችና ባርያዎች ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ ያደርጋል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሁለተኛው አውሬ ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፥ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች፥ ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች፥ ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 13:16
26 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈ​ልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገ​ደል ዘንድ ማሉ።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


ከክ​ብሩ ውበት ከጽ​ዮ​ንም፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነ​ኝና ለታ​ላ​ቁም፥ ለታ​ና​ሹም እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ እስከ ዛሬ ደረ​ስሁ፤ ይደ​ረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢ​ያት ከተ​ና​ገ​ሩት፥ ሙሴም ከተ​ና​ገ​ረው ሌላ ያስ​ተ​ማ​ር​ሁት የለም።


እኛ ሁላ​ች​ንም በአ​ንድ መን​ፈስ አንድ አካል ለመ​ሆን ተጠ​ም​ቀ​ናል፤ አይ​ሁድ ብን​ሆን፥ አረ​ማ​ው​ያ​ንም ብን​ሆን፥ ባሪ​ያ​ዎ​ችም ብን​ሆን፥ ነጻ​ዎ​ችም ብን​ሆን ሁላ​ችን አንድ መን​ፈስ ጠጥ​ተ​ና​ልና።


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።


ጌታም ቢሆን፥ አገ​ል​ጋ​ይም ቢሆን መል​ካም ያደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዋጋ እን​ደ​ሚ​ያ​ገኝ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


“እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ።


በእ​ጅ​ህም እንደ ምል​ክት አድ​ር​ገው፤ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁ​ን​ልህ።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።


አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”


በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ድምፅም “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤” ሲል ከዙፋኑ ወጣ።


ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።


ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።


የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኀይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዐለቶች ተሰወሩ፤


“የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos