Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አብድዩ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ሌቦች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ወይም ወን​በ​ዴ​ዎች በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ርቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወይ​ንም የሚ​ቈ​ርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃር​ሚያ አያ​ስ​ቀ​ሩ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን? አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ሌቦች ወይም ቀማኞች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤ የወይን ምርትንም የሚሰበስቡ ቃርሚያ ይተዋሉ፤ የአንተ ጠላቶች ግን ፈጽሞ ያጠፉሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን የሚሰርቁ አይደሉምን? ወይንንም የሚቈርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ አያስቀሩምን?

Ver Capítulo Copiar




አብድዩ 1:5
13 Referencias Cruzadas  

ወይን ለቃ​ሚ​ዎች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ቃር​ሚ​ያ​ውን አይ​ተ​ዉ​ል​ህ​ምን? ሌቦ​ችስ በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​ያ​ጠ​ፉት እስ​ኪ​በ​ቃ​ቸው ድረስ አይ​ደ​ለ​ምን?


የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ በቈ​ረ​ጥህ ጊዜ ቃር​ሚ​ያ​ውን አት​ል​ቀ​መው፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ይሁን።


ወይራ በተ​መታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ቀር፥ አራት ወይም አም​ስት በዛ​ፊቱ ጫፍ እን​ደ​ሚ​ገኝ፥ በእ​ርሱ ዘንድ ቃር​ሚያ ይቀ​ራል” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ፈ​ጫት መዶሻ እን​ዴት ደቀ​ቀች! እን​ዴ​ትስ ተሰ​በ​ረች! ባቢ​ሎ​ንስ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ባድማ ሆነች!


ይህ ሁሉ በሀ​ገር ውስጥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይሆ​ናል። የወ​ይራ ፍሬ ለቀማ ባለቀ ጊዜ በቃ​ር​ሚ​ያው ውስጥ የወ​ይራ ፍሬ እን​ደ​ሚ​ለ​ቀም እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይቃ​ር​ሟ​ቸ​ዋል።


“አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ!


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ለሞ​ቱ​ትና ለተ​ገ​ደ​ሉት ሐው​ልት ትከል፤ ኀያ​ላን እን​ዴት ወደቁ!


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ወይ​ንን እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም፥ እን​ዲሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩ​ትን ይቃ​ር​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ እጅ​ህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እን​ቅብ ዘርጋ።


ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios