Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 4:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት ሆኗቸው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል የመጡት ወንዶች ሁሉ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገልግሎት የገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:35
15 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።


የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከሠ​ላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈ​ጠሩ ሠላሳ ስም​ንት ሺህ ነበረ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሥራ​ውን ለመ​ሥ​ራ​ትና ዕቃ​ውን ለመ​ሸ​ከም የገ​ቡት ሁሉ፥ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሯ​ቸው።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


ሙሴና አሮ​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቀ​ዓ​ትን ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios