Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 25:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ምድ​ያ​ማ​ዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ፤ እር​ስ​ዋም የሱር ልጅ ነበ​ረች፤ እር​ሱም የም​ድ​ያም አባ​ቶች ወገን የሚ​ሆን የሳ​ሞት ወገን አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንዲሁም የተገደለችዋ ምድያማዊት ሴት ከስቢ ትባላለች፤ እርሷም ከምድያማውያን ቤተ ሰብ የአንዱ ነገድ አለቃ የሆነው የሱር ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የተገደለችውም ምድያማዊት ስምዋ ከስቢ ትባል ነበረ፤ እርሷም የሱር ልጅ ነበረች፤ እርሱም በምድያም ዘንድ የአባቱ ቤት ወገን አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የሴቲቱም ስም ኮዝቢ ይባል ነበር፤ “ጹር” ተብሎ የሚጠራው አባትዋም በአንድነት የሚኖሩ የጥቂት ምድያማውያን ጐሣዎች አለቃ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የተገደለችውም ምድያማዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ፤ እርስዋም የሱር ልጅ ነበረች፤ እርሱም በምድያም ዘንድ የአባቱ ቤት ወገን አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 25:15
7 Referencias Cruzadas  

ሞዓ​ብም የም​ድ​ያ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “በሬ የለ​መ​ለ​መ​ውን ሣር እን​ደ​ሚ​ጨ​ርስ ይህ ሠራ​ዊት በዙ​ሪ​ያ​ችን ያለ​ውን ሁሉ ይጨ​ር​ሳል” አላ​ቸው። በዚ​ያን ጊዜ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ የሞ​ዓብ ንጉሥ ነበረ።


ከም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ቱም ጋር የተ​ገ​ደ​ለው የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ሰው ስም ዘን​በሪ ነበረ፤ የአ​ባቱ ቤት አለቃ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦


ስለ ምድ​ያም አለቃ ልጅ ስለ እኅ​ታ​ቸው ስለ ከስቢ በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት በሸ​ነ​ገ​ሉ​አ​ችሁ ሽን​ገላ አስ​ጨ​ን​ቀ​ዋ​ች​ኋ​ልና።”


የም​ድ​ያ​ም​ንም ነገ​ሥ​ታት በዚ​ያው ጦር​ነት በአ​ን​ድ​ነት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢ​ዖ​ር​ንም ልጅ በለ​ዓ​ምን ደግሞ በዚ​ያው ጦር​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


የሚ​ሶር ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገ​ሠው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እር​ሱ​ንና በም​ድ​ሪቱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የሴ​ዎ​ንን መሳ​ፍ​ንት፥ የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ኤዊን፥ ሮቦ​ቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲ​ዮን የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ገደ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድ​ያም እጅ ሰባት ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos