Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ይህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውን ውኃ የሚ​ረጭ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ው​ንም ውኃ የሚ​ነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ይህም ለእነርሱ የዘላለም ሥርዐት ነው። “የሚያነጻውን ውሃ የሚረጨውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ የሚያነጻውንም ውሃ የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማምሻው ድረስ የረከሰ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ይህም ለእነርሱ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ የሚረጨው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ከርኩሰትም የሚያነጻውን ውኃ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህን ሕግ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ ለማንጻት የሚያገለግለውን ውሃ በላዩ የሚረጨው ሰው ልብሱን ማጠብ ይኖርበታል፤ ውሃውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ያልነጻ ሆኖ ይቈያል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሆንላችኋል፤ የሚያነጻውን ውኃ የሚረጭ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ የሚያነጻውንም ውኃ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 19:21
12 Referencias Cruzadas  

የላ​ምና የፍ​የል ደም ኀጢ​አ​ትን ሊያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ አይ​ች​ል​ምና።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


ኦሪት ምንም ግዳጅ አል​ፈ​ጸ​መ​ች​ምና፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ፋንታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ቀ​ር​ብ​በት ከእ​ር​ስዋ የሚ​ሻል ተስፋ ገብ​ቶ​አል።


ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድን የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።


ሌዋ​ው​ያን ግን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ይሥሩ፤ እነ​ር​ሱም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አይ​ወ​ር​ሱም።


ያቃ​ጠ​ላ​ትም ሰው ልብ​ሱን በውሃ ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።


የጊ​ደ​ሪ​ቱ​ንም አመድ ያከ​ማ​ቸው ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios