ነህምያ 3:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 ከእርሱም በኋላ የሰራፊ ልጅ መልክያ እስከ ናታኒምና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት ድረስ በሐሜፍቃድ በር አንጻር ያለውን እስከ ማዕዘኑ መውጫ ድረስ ሠራ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ከርሱ ቀጥሎ ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ መልክያ በመቈጣጠሪያው በር ትይዩ እስከሚገኘው እስከ ቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት፣ እንዲሁም ከማእዘኑ በላይ እስከሚገኘው ክፍል ያለውን መልሶ ሠራ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ከእርሱም በኋላ የወርቅ አንጥረኛው ልጅ ማልኪያ ከ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ቤት፥ የነጋዴዎቹ ቤት ጀምሮ እስከ “የመሰብሰቢያ በር” ፊት ለፊት ያለውንና እስከ ማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ድረስ አደሰ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ወርቅ አንጥረኛው ማልኪያ ተከታዩን መስመር ከቅጽሩ ማእዘን ሰሜናዊ ምሥራቅ ጫፍ አጠገብ እስካለው መቈጣጠሪያ ቅጽር በር በኩል የቤተ መቅደሱ ሠራተኞችና ነጋዴዎች እስከሚገለገሉበት ስፍራ ድረስ ሠራ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 ከእርሱም በኋላ ከወርቅ አንጥረኞቹ የነበረ መልክያ እስከ ናታኒምና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት ድረስ በሐሚ ፍቃድ በር አንጻር ያለውን እስከ ማዕዘኑ መውጫ ድረስ አደሰ። Ver Capítulo |