Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፤አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመሪያ ሄደህ ከወንድምህ ጋራ ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 መባህን እዚያው በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፤ አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ ከዚያ በኋላ መጥተህ መባህን አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 መባህን በመሠዊያው ፊት አስቀምጥና፥ ሄደህ በመጀመሪያ ከዚያ ከወንድም ጋር ታረቅ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰህ መባህን አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 5:24
13 Referencias Cruzadas  

እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


አሁን እን​ግ​ዲህ ሰባት ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዛ​ችሁ ወደ ባሪ​ያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ እር​ሱም የሚ​ቃ​ጠ​ልን መሥ​ዋ​ዕት ስለ ራሳ​ችሁ ያሳ​ር​ግ​ላ​ችሁ። ባሪ​ያ​ዬም ኢዮብ ስለ እና​ንተ ይጸ​ልይ፥ እኔም ፊቱን እቀ​በ​ላ​ለሁ። ስለ እርሱ ባይ​ሆን ባጠ​ፋ​ኋ​ችሁ ነበር። በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና።”


እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።


አሁ​ንም ሰው ራሱን መር​ም​ሮና አን​ጽቶ ከዚህ ኅብ​ስት ይብላ፤ ከዚ​ህም ጽዋ ይጠጣ።


ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”


እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios